Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መክብብ 10:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፥ እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የሞቱ ዝንቦች ሽቱን እንደሚያገሙ፣ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብንና ክብርን ያቀልላል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሞቱ ዝንቦች ተቀምሞ የተሠራውን የዘይት ሽቶ ሊያገሙት ይችላሉ፤ እንዲሁም ትንሽ ሞኝነት ታላቅ ጥበብን ያጠፋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የሞቱ ዝን​ቦች የተ​ቀ​መ​መ​ውን የዘ​ይት ሽቱ ያገ​ሙ​ታል፤ በስ​ን​ፍ​ናም ካለ ታላቅ ክብር ይልቅ ትንሽ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፥ እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል።

See the chapter Copy




መክብብ 10:1
11 Cross References  

የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በዚህ ነገር ኃጢአት አድርጎ የለምን? በብዙ አሕዛብም መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፥ በአምላኩም ዘንድ የተወደደ ነበረ፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ሁሉ ላይ አንግሦት ነበር፥ እርሱንም እንኳ እንግዶች ሴቶች አሳቱት።


ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፥ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ ጌታን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከጌታ ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል።


በቀማሚ እንደሚቀመም ቅመም የተቀደሰ የቅባት ዘይት ታደርገዋለህ፤ የተቀደሰ የቅባት ዘይትም ይሆናል።


ይህንም ነገር አደርግና እበድል ዘንድ፥ በእኔም ላይ ክፋት እንዲናገሩና እንዲያላግጡ ያስፈራራኝ።


ከባሕር አሸዋ ይልቅ በከበደ ነበርና፥ ለዚህም ነው ቃሌ ደፋር የሆነው።


ከጦር መሣሪያዎች ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፥ አንድ ኃጢአተኛ ግን ብዙ መልካምን ያጠፋል።


አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዕጥፋት ቢይዝ፥ ዕጥፋቱ እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውንም መብል ቢነካ ያ የተነካው የተቀደሰ ይሆናልን? ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ።


ሐጌም፦ በሬሳ የረከሰ ሰው ከእነዚህ አንዱን ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይረክሳልን? አለ። ካህናቱም፦ አዎን ይረክሳል ብለው መለሱ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements