ዘዳግም 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ በመነሳቱ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ። ጌታ ግን ልመናዬን ደግሞ ሰማኝ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እናንተን ሊያጠፋችሁ ክፉኛ ተቈጥቶ ነበርና፣ እኔም የእግዚአብሔርን ቍጣና መዓት ፈራሁ፤ እግዚአብሔር ግን እንደ ገና ሰማኝ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 በመዓቱም ሊደመስሳችሁ ስለ ተነሣሣ የእግዚአብሔር ብርቱ ቊጣ አስፈርቶኝ ነበር፤ ነገር ግን እንደገና እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ ከተቈጣባችሁ ከቍጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ፤ እግዚአብሔርም በዚያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ። See the chapter |