ዘዳግም 9:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ተመለከትሁም፥ እነሆ፥ አምላካችሁን ጌታ በድላችሁ ነበር፥ ለእናንተም ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር፤ ጌታ ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 በርግጥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርታችሁ እንደ ነበር ተመለከትሁ፤ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስልም ለራሳችሁ አበጃችሁ፤ እግዚአብሔር እናንተን ካዘዛችሁ መንገድ በፍጥነት ወጥታችሁ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰጣችሁ ትእዛዝ ወዲያው ፈቀቅ ብላችሁ፥ ወርቅ አቅልጣችሁ በጥጃ ምስል ጣዖት በመሥራት በእግዚአብሔር ላይ ማመፃችሁን ተመለከትኩ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እነሆ፥ በአምላካችሁ እግዚአብሔር ፊት እንደ በደላችሁ፥ ለእናንተም ቀልጦ የተሠራ ምስል ሠርታችሁ ልትጠብቁት እግዚአብሔር ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ፈቀቅ እንዳላችሁ ባየሁ ጊዜ፥ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ተመለከትሁም፤ እነሆ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በድላችሁ ነበር፥ ለእናንተም ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር፤ እግዚአብሔር ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር። See the chapter |