ዘዳግም 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ጌታም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፥ ተሰብስባችሁ በነበረበትም ቀን ጌታ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የነገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላት እግዚአብሔር ሰጠኝ፤ በተሰበሰባችሁበት ዕለት እግዚአብሔር ከተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የነገራችሁ ትእዛዞች ሁሉ በእነርሱ ላይ ነበሩባቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ከዚያም በኋላ እናንተ በተራራው ግርጌ በተሰበሰባችሁ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሰማችሁትን ቃል በእጁ የጻፈባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን ሁለት የድንጋይ ጽላት ሰጠኝ፤ በተሰበሰባችሁ ጊዜ እግዚአብሔር በተራራው ላይ የነገረኝ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፤ ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የነገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። See the chapter |