ዘዳግም 6:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ለእናንተ ያዘዘውን የጌታ የአምላካችሁን ምስክሩን፥ ሥርዓቱንም፥ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ያዙ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዞች፣ ምስክርነቶችና ሥርዐቶች በጥንቃቄ ጠብቁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እርሱ ያዘዛችሁንም ትእዛዞች፥ ድንጋጌዎችና ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ጠብቁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ለአንተ ያዘዘውን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ፥ ምስክሩንም፥ ሥርዐቱንም አጥብቀህ ጠብቅ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ለእናንተ ያዘዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ምስክሩንም ሥርዓቱንም አጥብቃችሁ ጠብቁ። See the chapter |