Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 4:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች የተናገረው ምስክርና ሥርዓት፥ ሕጎችም እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ምስክርነቶች፣ ሥርዐቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤላውያን ያስተላለፈላቸው ድንጋጌዎች፥ ሕጎችና ደንቦች ከዚህ በላይ ያሉት ናቸው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ና​ገ​ረው ምስ​ክ​ርና ሥር​ዐት፤ ፍር​ድም ይህ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45-46 ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመቱት፥ በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አንጻር ባለው ሸለቆ በዮርዳኖስ ማዶ፥ ከግብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች የተናገረው ምስክርና ሥርዓት ፍርድም ይህ ነው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 4:45
13 Cross References  

የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።


ሕግህም ተድላዬ ነው፥ ደንቦችህም አማካሪዎቼ ናቸው።


ሕግህን ጠብቄአለሁና። ስድብንና ነውርን ከእኔ አርቅ።


በብልጽግና እንደሚደሰቱ ሁሉ በሕጎችህ መንገድ ደስ አለኝ።


አቤቱ፥ ትክክለኛ ፍርድህን ስማር በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።


ደንቦችህን ለመጠበቅ መንገዶቼ ምነው በቀኑ።


ሕጉን የሚጠብቁ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ምስጉኖች ናቸው፥


አምላክህ ጌታ እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤


“በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፥ ‘አምላካችን ጌታ ያዘዛችሁ ምስክርነቶች፥ ሥርዓት፥ ፍርድስ ምንድነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥


ለእናንተ ያዘዘውን የጌታ የአምላካችሁን ምስክሩን፥ ሥርዓቱንም፥ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ያዙ።


“አሁንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው በሕይወትም እንድትኖሩ፥ የአባቶቻችሁም አምላክ ጌታ ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ የማስተምራችሁን ሥርዓትና ሕግጋት ስሙ።


ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት።


ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ በኋላ ድል በነሱት፥ በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፥ በቤተፌዖር አንጻር ባለው ሸለቆ በዮርዳኖስ ማዶ ያወጃቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements