Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 33:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ለአንት ሲል እናቱንና አባቱን፥ ‘አላየሁም’ ላለ፥ ወንድሞቹንም ላላስተዋለ፥ ልጆቹንም ላላወቀ፥ ቃልህን ላከበረ፥ ቃል ኪዳንህንም ለጠበቀ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፣ ‘ስለ እነርሱ ግድ የለኝም’ አለ። ወንድሞቹን አልለያቸውም፤ ልጆቹንም አላወቃቸውም። ለቃልህ ግን ጥንቃቄ አደረገ፤ ኪዳንህንም ጠበቀ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እነርሱ ለአንተ ሲሉ ወላጆቻቸውን ረስተዋል፤ ከዘመዶቻቸው ተለይተዋል፤ ልጆቻቸውን ትተዋል፤ ቃልህን አክብረዋል። ቃል ኪዳንህንም ጠብቀዋል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እና​ቱ​ንና አባ​ቱን አላ​የ​ኋ​ች​ሁም ላለ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ላላ​ወቀ፥ ልጆ​ቹ​ንም ላላ​ስ​ተ​ዋለ፤ ቃል​ህን ለጠ​በቀ፥ በቃል ኪዳ​ን​ህም ለተ​ማ​ጠነ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ስለ አባቱና ስለ እናቱ፦ አላየሁም ላለ፥ 2 ወንድሞቹንም ላላስተዋለ፥ 2 ልጆቹንም ላላወቀ፤ 2 ቃልህን አደረጉ፥ 2 ቃል ኪዳንህንም ጠበቁ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 33:9
17 Cross References  

“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።


እርሱ ግን ለነገረው መልሶ እንዲህ አለው “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አለው።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔም ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


አሁን ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሳምናለሁን? ወይስ ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? እስከ አሁን ሰውን ደስ የማሰኝ ብሆን ኖሮ የክርስቶስ ባርያ አልሆንም ነበር።


ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።


ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ላኩበት፤ እነርሱም እንዱህ አሉት “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደሆንህ የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አታይምና፤


እነርሱም፦ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፥ በኤርምያስ ላይ ሤራን እናሢር። ኑ፥ በአንደበት እንምታው፥ ቃላቱንም ሁሉ አናድምጥ” አሉ።


ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል፥ በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም።”


አምላክ ሆይ! ይህ በፊትህ ጥቂት የሆነ ነገር ነበረ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ስለ ባርያህ ቤት ደግሞ ስለ ወደ ፊቱ ሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ።


በድንም ወደ አለበት ስፍራ ሁሉ አይሂድ፥ ስለ አባቱም ወይም ስለ እናቱ አይርከስ።


ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እንዳትሞቱ በማኅበሩም ሁሉ ላይ እርሱ እንዳይቈጣ የራሳችሁን ጠጉር አታጐስቁሉ፥ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ጌታ እሳትን ልኮ ስላደረገው ማቃጠል ግን ወንድሞቻችሁ የእስራኤል ቤት ሁሉ ያልቅሱ።


ልያም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና።


አንዱን ከሌላው በማበላለጥ ምንም ዓይነት ነገር ሳታደርግ፥ ያለ አድልዎ እነዚህን ትዛዛቶች እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ በተመረጡትም መላእክት ፊት አደራ እልሃለሁ።


ነገር ግን ወንጌል በአደራ እንዲሰጠን እግዚአብሔር የታመንን እንዳደረገን፥ እንዲሁ ሰውን ደስ ለማሰኘት ሳይሆን ልባችንን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ብለን እንናገራለን።


ጌታ ድርሻዬ ነው፥ ቃልህን እጠብቃለሁ አልሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements