ዘዳግም 33:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፥ በጌታ የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፥ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ብፁዕ ነህ፤ አንተ እስራኤል ሆይ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፣ እንደ አንተ ያለ ማን አለ? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፣ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ በፍርሀት ከፊትህ ያፈገፍጋሉ፤ አንተም የማምለኪያ ኰረብታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 እስራኤል ሆይ! የእርዳታህ ጋሻ፥ የድልህ ሰይፍ መዳንን ከእግዚአብሔር ያገኘ፥ እንዳንተ ያለ ሕዝብ ከቶ የለም፤ ምንኛ የታደልክ ነህ! ጠላቶች እየተለማመጡ ወደ አንተ ሲመጡ ጀርባቸውን ትረግጣለህ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 እስራኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማንነው? እርሱ ያጸንሃል፤ ይረዳሃልም፤ ትምክሕትህ በሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ ውሸታሞች ናቸው፤ አንተም በአንገታቸው ላይ ትጫናለህ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ 2 በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? 2 እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ 2 የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። 2 ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ 2 አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ። See the chapter |