ዘዳግም 33:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እንዲህም አለ፦ “ጌታ ከሲና ተራራ መጣ፥ በሴይርም እንደ ንጋት ተገለጠ፥ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ በስተቀኙም ከእሳት ነበልባል ጋር፥ ከአእላፋት ቅዱሳኑም ጋር መጣ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሓይ ወጣ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋራ መጣ፤ በስተ ቀኙ የሚነድድ እሳት ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ሙሴም እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጣ፤ ከኤዶም ላይ እንደ ንጋት ፀሐይ አበራ፤ ከፋራንም ተራራ ላይ አንጸባረቀ፤ በስተቀኙ የእሳት ነበልባል ነበር፤ ከእርሱም ጋር አእላፍ መላእክት ነበሩ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በሴይርም ተገለጠልን፤ ከፋራን ተራራ፥ ከቃዴስ አእላፋት ጋር ፈጥኖ መጣ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር በቀኙ ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እንዲህም አለ፦ 2 እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥ 2 በሴይርም ተገለጠ፤ 2 ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ 2 ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤ 2 በስተቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው። See the chapter |