ዘዳግም 32:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ የሰውን ልጆች በለየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቍጥር የአሕዛብን ድንበር አቆመ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ፣ የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፣ በእስራኤል ልጆች ቍጥር ልክ፣ የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥ የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥ ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ልዑል አሕዛብን በከፈላቸው ጊዜ፥ የአዳምንም ልጆች በለያቸው ጊዜ፥ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቍጥር፥ አሕዛብን በየድንበራቸው አቆማቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ 2 የአዳምን ልጆች በለየ ጊዜ፥ 2 እንደ እስራኤል ልጆች ቁጥር 2 የአሕዛብን ድንበር አቆመ። See the chapter |