ዘዳግም 32:51 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)51 ምክንያቱም ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ፥ በቃዴስ በመሪባ ውሃ አጠገብ በእኔ ላይ መታመናችሁን በእስራኤላውያን ፊት ስላጐደላችሁና ቅድስናዬንም በእስራኤላውያን መካከል ስላላከበራችሁ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም51 ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ፣ በቃዴስ መሪባ ውሃ አጠገብ በእኔ ላይ መታመናችሁን በእስራኤላውያን ፊት ስላጐደላችሁና ቅድስናዬንም በእስራኤላውያን መካከል ስላላከበራችሁ ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም51 እናንተ ሁለታችሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ለእኔ ታማኞች ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ከተማ አጠገብ በምትገኘው በመሪባ ውሃ ምንጮች አጠገብ በነበራችሁበት ጊዜ በእስራኤል ሕዝብ ፊት እንድከበር አላደረጋችሁም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)51 በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በክርክር ውኃ ለቃሌ አልታዘዛችሁምና፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል አልቀደሳችሁኝምና፥ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)51 በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውኃ ስለ በደላችሁኝ፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል ስላልቀደሳችሁኝ፥ See the chapter |