Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 32:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተሰበሰበ ሁሉ፥ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፥ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተሰበሰበ ሁሉ፣ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ ሞቶ ወደ ወገኖቹ እንደ ተቀላቀለ አንተም በዚሁ በነቦ ተራራ ላይ ሞተህ ከወገኖችህ ጋር ትቀላቀላለህ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 ወን​ድ​ምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ፥ ወደ ወገ​ኖ​ቹም እንደ ተጨ​መረ፥ በወ​ጣ​ህ​በት ተራራ ሙት፤ ወደ ወገ​ኖ​ች​ህም ተጨ​መር፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 ወንድምህም አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ ወደ ወገኖቹም እንደ ተከማቸ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፥ ወደ ወገኖችህም ተከማች፤

See the chapter Copy




ዘዳግም 32:50
12 Cross References  

በመጨረሻዋ እስትንፋሱ አብርሃም ነፍሱን ሰጠ፥ በመልካምም ሽምግልና ሞተ፥ ሸምግሎ፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።


ካህኑም አሮን በጌታ ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።


ያዕቆብም ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹን በአልጋ ላይ ሰብስቦ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።


እስማኤልም የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው፥ የመጨረሻዋ እስትንፋሱን ተንፍሶም ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።


አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፥ በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ።


ጌታ ሙሴን፥ “እነሆ የምትሞትበት ቀን ቀርቧል፤ ትእዛዝ እንድሰጠው ኢያሱን ጥራውና ወደ መገናኛው ድንኳን ቅረቡ።” ሙሴና ኢያሱም ሄዱ፤ ወደ መገናኛው ድንኳንም ቀረቡ።


የጌታ ባርያም ሙሴ እንደ ጌታ ቃል በሞዓብ ምድር ሞተ።


ስማቸውም የተለወጠውን ናባውን፥ በኣልሜዎንን፥ ሴባማን ነበር፤ እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች በሌላ ስም ጠሩአቸው።


ከሐሽሞናም ተጉዘው በሞሴሮት ሰፈሩ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements