ዘዳግም 32:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 በሚያቃጥል ንዳድና በራብ ያልቃሉ፤ በወረርሽኝ መቅሠፍት ይጠፋሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችን፥ ከሚሳቡ መርዘኛ እባቦችን ጋር እሰድባቸዋለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 የሚያጠፋ ራብ፣ በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድድባቸዋለሁ፤ የአራዊትን ሹል ጥርስ፣ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድድባቸዋለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 የሚጨርስ ራብ በእነርሱ ላይ እልካለሁ፤ በወረርሽኝና በመቅሠፍት ያልቃሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችንና መርዘኛ ተናዳፊ እባቦችን እሰድባቸዋለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 በራብ ያልቃሉ፤ ለሰማይ ወፎችም መብል ይሆናሉ፤ ኀይላቸውም ይደክማል፥ ከምድር ይጠፉ ዘንድ የምድር አራዊትን ጥርስ፥ ከመርዝ ጋር እልክባቸዋለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 በራብ በንዳድ ይጠፋሉ፤ 2 በንዳድና በመራራ ጥፋት ያልቃሉ፤ 2 የአራዊትን ጥርስ፥ 2 የምድርንም እባብ መርዝ እሰድድባቸዋለሁ። See the chapter |