ዘዳግም 32:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ንስር ጎጆዋን ቆስቁሳ፥ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ይወስደዋል፥ በክንፎቹም ያዝለዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ንስር ጐጆዋን በትና፣ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፣ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ፣ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፣ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 በጫጩቶችዋ ላይ እንደምታንዣብብ፥ ጎጆዋን እንደምትጠብቅ ንስር፥ እርሱን ለመያዝ ክንፎቹን ይዘረጋል፤ በክንፎቹም ጫፍ ይደግፈዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ንስር ጫጩቶቹን በክንፎቹ በታች እንደሚሰበስብ፥ በጎኑም እንደሚያቅፍ፥ በክንፎቹ አዘላቸው፤ በደረቱም ተሸከማቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ 2 በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ 2 ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ 2 በክንፎቹም አዘላቸው። See the chapter |