ዘዳግም 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ኢያሱንም ያንጊዜ አዘዝኩት፦ “ጌታ አምላካችሁ በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ያደረገውን ሁሉ ዐይኖችህ አይተዋል፥ እንዲሁ ሁሉ በምታልፍባቸው መንግሥታት ላይ ጌታ ያደርጋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 በዚያ ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ስል አዘዝሁት፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ በገዛ ዐይንህ አይተሃል፤ አሁንም ዐልፈህ በምትሄድባቸው መንግሥታት ላይ ሁሉ እግዚአብሔር ይህንኑ ይደግመዋል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 “ከዚህም ቀጥሎ ኢያሱን እንዲህ ስል መከርኩት፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ ሲሖንና ዖግ ተብለው በሚጠሩት በሁለት ነገሥታት ያደረገውን በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ምድሩን በምትወርሱበት በማንኛውም ሕዝብ ላይ ይህንኑ ተመሳሳይ ድርጊት ይደግመዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 በዚያም ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ብዬ አዘዝሁት፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥት ያደረገውን ሁሉ ዐይኖችህ አይተዋል፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታት ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 በዚያም ጊዜ ኢያሱን፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥት ያደረገውን ሁሉ ዓይኖችህ አይተዋል፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታት ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል። See the chapter |