ዘዳግም 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ ባሳንን ሁሉ፥ እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ድረስ፥ በባሳንም ያሉትን የዖግን መንግሥት ከተሞች ወሰድን። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በከፍታው ቦታ ላይ የሚገኙትን ከተሞች በሙሉ፣ ገለዓድን እንዳለ፣ እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ያለውን ባሳንን ሁሉ እንዲሁም በባሳን ውስጥ የሚገኙትን የዐግ ግዛት ከተሞች በእጃችን አደረግን። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 በዚህም ዐይነት የባሳን ንጉሥ የዖግ ግዛቶች የሆኑትን በደጋ የሚገኙትን ሳለካና ኤድረዒ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና እንዲሁም የገለዓድንና የባሳንን አውራጃዎች ሁሉ ያዝን። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 የሚሶርንም ከተሞች ሁሉ፥ የገለዓድንም ሁሉ፥ የባሳንንም ሁሉ እስከ ኤልከድና እስከ ኤድራይን ድረስ በባሳን የሚኖር የዐግን መንግሥት ከተሞች ሁሉ ወሰድን። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ በባሳንም ያሉትን የዐግን መንግሥት ከተሞች እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ድረስ ባሳንን ሁሉ ወሰድን። See the chapter |