Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 29:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ለአንተ በሰጠው ተስፋና ለአባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት እርሱ አምላክህ ይሆን ዘንድ፥ አንተም ሕዝቡ መሆንህን፥ በዛሬው ዕለት ለማረጋገጥ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ለአንተ በሰጠው ተስፋና ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት እርሱ አምላክህ ይሆን ዘንድ፣ አንተም ሕዝቡ መሆንህን በዛሬው ዕለት ለማረጋገጥ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር ይህን ያደረገው በሰጣችሁ ተስፋና ለአባቶቻችሁም ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብ በመሐላ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት እናንተን የራሱ ሕዝብ አድርጎ ሊመሠርታችሁ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዛሬ ለእ​ርሱ ሕዝብ ያደ​ር​ግህ ዘንድ፥ እር​ሱም ለአ​ንተ እንደ ተና​ገረ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እንደ ማለ አም​ላክ ይሆ​ን​ልህ ዘንድ ነው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 29:13
12 Cross References  

ለእኔ ሕዝብ አድርጌ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብጽ ጭቆና ያወጣኋችሁ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።


“የጌታ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የምትጠብቅና በመንገዱ የምትሄድ ከሆነ፥ እንደ ማለልህ ለእርሱ የተቀደሰ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል።


አሁን ግን የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና አምላካቸው ተብሎ ለመጠራት በእነርሱ አያፍርም።


እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


“ለጌታ አምላክህ አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ፥ ጌታ አምላክህ ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ እንድትሆን መረጠህ።


በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”


እዚህ የቆምኸው ጌታ ዛሬ ከአንተ ጋር ወደሚያደርገውና በመሓላ ወደሚያጸናው ኪዳን ከጌታህ ከእግዚአብሔር ጋር ትገባ ዘንድ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements