Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 29:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እዚህ የቆምኸው ጌታ ዛሬ ከአንተ ጋር ወደሚያደርገውና በመሓላ ወደሚያጸናው ኪዳን ከጌታህ ከእግዚአብሔር ጋር ትገባ ዘንድ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እዚህ የቆምኸው እግዚአብሔር ዛሬ ከአንተ ጋራ ወደሚያደርገውና በመሐላ ወደሚያጸናው ኪዳን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ጋራ ትገባ ዘንድ፣

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የቆማችሁትም ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ነው፤ ይህም ቃል ኪዳን እግዚአብሔር አምላካችሁ ዛሬ ለእናንተ በመሐላ ያረጋገጠው ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ይኸ​ውም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ዛሬ በሚ​ያ​ደ​ር​ገው ቃል ኪዳ​ንና አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር በተ​ማ​ማ​ለው መሐላ ትገባ ዘንድ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12-13 ይኸውም ዛሬ ለእርሱ ሕዝብ አድርጎ ያስነሣህ ዘንድ፥ እርሱም ለአንተ እንደ ተናገረ ለአባቶችህም ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንደ ማለ አምላክ ይሆንልህ ዘንድ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ዛሬ በሚያደርገው ቃል ኪዳን ትገባ ዘንድና የአምላክህን የእግዚአብሔርን መሐላ ትሰማ ዘንድ ነው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 29:12
14 Cross References  

ዮዳሄ፥ ንጉሡና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፤ እንዲሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ።


በዚያም ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፥ በሴኬምም ሥርዓትና ፍርድ አደረገላቸው።


“እኔም ይህን የመሓላ ኪዳን የማደርገው ከእናንተ ጋር ብቻ አይደለም፤


ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ፥ በሰፈራችሁም ያለ እንጨትህን የሚቆርጥ ውኃህንም የሚቀዳ መጻተኛ አብረውህ ቆመዋል።


ለአንተ በሰጠው ተስፋና ለአባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት እርሱ አምላክህ ይሆን ዘንድ፥ አንተም ሕዝቡ መሆንህን፥ በዛሬው ዕለት ለማረጋገጥ ነው።


ለእኔ የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወስደሽ ለእነርሱ መብል እንዲሆኑ ሠዋሻቸው። አመንዝራነትሽ አንሶ ነውን?


ለእኔ ሕዝብ አድርጌ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብጽ ጭቆና ያወጣኋችሁ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


እነሆ፥ ምድሪቱን በፊታችሁ አኖራለሁ፥ ግቡ፥ ጌታ ለእነርሱ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውንም ምድር ውረሱ።’


ጌታ አምላክህ እንደሆነ በመንገዱም እንደምትሄድ፥ ሥርዓቱን፥ ትእዛዙንና ሕጉን እንደ ምትጠብቅና እንደምትታዘዝለት ተናግረሃል።


“የጌታ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የምትጠብቅና በመንገዱ የምትሄድ ከሆነ፥ እንደ ማለልህ ለእርሱ የተቀደሰ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements