Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 28:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “ጌታ በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ጠላቶችህ በአንተ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ እግዚአብሔር እነርሱን ድል ያደርግልሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ይሸሻሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ግ​ርህ በታች ይወ​ድቁ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ህን ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ በሰ​ባ​ትም መን​ገድ ከፊ​ትህ ይሸ​ሻሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፥ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 28:7
21 Cross References  

ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም፥ የዓመፃ ልጅም መከራ አይጨምርበትም።


ኢዮሣፍጥም በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ ዳግመኛም ከቤር-ሳቤህ ጀምሮ እስከ ተራራማው እስከ ኤፍሬም አገር ድረስ ወደ ሕዝቡ ወጥቶ ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ ጌታ መለሳቸው።


ሌሎቹም በእነርሱ ላይ ከከተማይቱ ወጡ፤ የጋይም ሰዎች በእስራኤል መካከል ሆኑ፥ እስራኤልም ከበቡአቸው፤ አንድ እንኳ ሳይቀር ሳያመልጥም ገደሉአቸው።


“ጌታ በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ በሚደርስብህም ነገር ለምድር መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ።


የእስራኤልም አምላክ ጌታ ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ።


እርሱ አንባቸው ካልሸጣቸው፥ ጌታም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ እንዴት አንዱ ሺህን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺህ ያባርራሉ?


“ስትገባ ትባረካለህ፤ ስትወጣም ትባረካለህ።


“ጌታ በጐተራህና እጅህ በነካው ሁሉ ላይ በረከቱን ይልካል። ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ላይ ይባርክሃል።


ጌታ አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና ከእናንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል።


ከዚህም በኋላ ቀኑ ሊመሽ ሲል ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄዱ፤ ነገር ግን እዚያ ሲደርሱ ማንም ሰው አልነበረም፤


ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements