| ዘዳግም 28:55 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)55 ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ታህል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ምክንያቱም ከተሞችህ ሁሉ ጠላቶችህ ከበው ከሚያደርሱብህ ሥቃይ የተነሣ ከዚህ በቀር የተረፈው የለም።See the chapter አዲሱ መደበኛ ትርጒም55 ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ታኽል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ከተሞችህ ሁሉ በመከበባቸው ጠላቶችህ ከሚያደርሱብህ ሥቃይ የተነሣ ለርሱ የቀረለት ይህ ብቻ ነውና።See the chapter አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም55 በዚያ ተስፋ በሚያስቈርጠው በከተሞችህ ሁሉ ላይ በሚደረገው በጠላት ከበባ ወቅት ሌላ ምንም የሚበላው ነገር ስለሌለው ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለማናቸውም አይሰጥም።See the chapter የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)55 በከተሞችህ ሁሉ ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀረው የለምና ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)55 በደጆችህ ሁሉ ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀረው የለምና ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም።See the chapter |