ዘዳግም 28:51 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)51 እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬና የምድርህን ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ የእህል፥ የወይን ወይም የዘይት፥ የከብትህን ጥጃ ወይም የበግና ፍየል መንጋህን አይተውልህም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም51 እስክትጠፋም ድረስ የእንስሳትህን ግልገልና የምድርህን ሰብል ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅ ሆነ ዘይት፣ የመንጋህን ጥጃ ሆነ የበግና የፍየል መንጋህን ግልገል አያስቀርልህም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም51 እነርሱ ከብትህንና ሰብልህን ሁሉ ጠራርገው ስለሚበሉት እስክትሞት ድረስ በራብ ትቸገራለህ። እነርሱ አንተ እስክትጠፋ ድረስ ከእህልህ አንዲት ፍሬ፥ ከከብትህ ጥጃ፥ ከበጎችህ መንጋ ጠቦት ከወይንህና ከወይራ ዛፍህ ቅንጣት ፍሬ እንኳ አያስተርፉልህም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)51 እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬ፥ የምድርህንም ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ እህልህን፥ ወይንህንም፥ ዘይትህንም፥ የላምህንና የበግህንም መንጋ አይተውልህም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)51 እስክትጠፋ ድረስ የከብትህን ፍሬ የምድርህንም ፍሬ ይበላሉ፤ እስኪያጠፉህም ድረስ እህልን የወይንም ጠጅ ዘይትንም የላምህንና የበግህን ርቢ አይተዉልህም። See the chapter |