ዘዳግም 28:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)45 “ጌታ እግዚአብሔርን ስላልታዘዝህና የሰጠህን ትእዛዝና ሥርዓት ስላልጠበቅህ እነዚህ ርግማኖች ሁሉ በአንተ ላይ ይመጣሉ፥ እስክትጠፋ ድረስ ያሳድዱህማል፥ ይወርሱሃል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም45 እነዚህ ርግማኖች ሁሉ በአንተ ላይ ይመጣሉ፤ አምላክህን እግዚአብሔርን ስላልታዘዝህና የሰጠህን ትእዛዝና ሥርዐት ስላልጠበቅህ እስክትጠፋ ድረስ ይከተሉሃል፤ ይወርዱብሃልም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም45 “አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ታዛዥ ሆነህ ስላልተገኘህና እርሱ የሰጠህን ደንቦችና ትእዛዞች ስላልጠበቅህ እነዚህ ሁሉ መቅሠፍቶች ይመጡብሃል፤ ፈጽሞ እስከምትደመሰስ ድረስ ከአንተ አይርቁም፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)45 የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ስላልሰማህ፥ ያዘዘህንም ትእዛዙንና ሥርዐቱን ስላልጠበቅህ፥ እስክትጠፋ ድረስ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይወርዱብሃል፤ ያሳድዱህማል፤ ያገኙህማል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)45 የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ስላልሰማህ፥ ያዘዘህንም ትእዛዙንና ሥርዓቱን ስላልጠበቅህ፥ እስክትጠፋ ድረስ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይወርዱብሃል፥ ያሳድዱህማል፥ ያገኙህማል። See the chapter |