Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 28:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 በሬህ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ አንዳች ግን አትቀምሰውም። አህያህም በግድ ይወሰድብሃል፤ ለአንተም አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚረዳህ ማንም አይኖርም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 በሬህ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ ከሥጋውም አንዳች አትቀምስም። አህያህም በግድ ይወሰድብሃል፤ አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚያስጥላቸውም አይኖርም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ከብትህ በፊትህ፥ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ ነገር ግን ከሥጋው አትቀምስም፤ አህዮችህ በፊትህ ተስበው ይወሰዳሉ፤ ነገር ግን አይመለሱልህም፤ በጎችህ ለጠላቶችህ ተላልፈው ይሰጣሉ፤ እነርሱን ለማዳን የሚረዳህም የለም፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 በሬህ በፊ​ትህ ይታ​ረ​ዳል፤ ከእ​ር​ሱም አት​በ​ላም። አህ​ያህ ከእ​ጅህ በግድ ይወ​ሰ​ዳል፤ ወደ አን​ተም አይ​መ​ለ​ስም፤ በጎ​ችህ ለጠ​ላ​ቶ​ችህ ይሰ​ጣሉ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም አታ​ገ​ኝም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 በሬህ በፊትህ ይታረዳል፥ ከእርሱም አትበላም፤ አህያህ ከእጅህ በግድ ይወሰዳል፥ ወደ አንተም አይመለስም፤ በግህ ለጠላቶችህ ትሰጣለች፥ የሚያድንህም አታገኝም።

See the chapter Copy




ዘዳግም 28:31
8 Cross References  

እንደገና እስራኤላውያን በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ጌታም ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰባት ዓመት ገዟቸው።


“ሚስት ለማግባት ታጫለህ፤ ሌላም ሰው ከእርሷ ጋር ይተኛል። ቤት ትሠራለህ፥ ግን አትኖርበትም። ወይን ትተክላለህ፤ ፍሬውን ግን አትበላም።


ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን ምንም ለማድረግ አትችልም፤ ከዛሬ ነገ ይመጣሉ በማለትም ዐይኖችህ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።


እነርሱም በምድሪቱ ላይ ሰፍረው እስከ ጋዛ ያለውን ሰብል በማጥፋት አንዳችም የእህልዘር አያስተርፉም፥ የበግም ሆነ የከብት ወይም የአህያ መንጋ አይተዉም ነበር።


የቤቱም ንብረት ይሰናበታል፥ በቁጣው ቀን በጐርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል።


ጌታ፦ ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም፤


መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም ይበላሉ፤ የምትተማመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደመስሳሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements