Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 26:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚያም ወቅት ለሚያገለግለው ካህን፥ ‘ጌታ ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደገባሁ ዛሬ በጌታ እግዚአብሔር ፊት እናገራለሁ’ በለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚያም ወቅት ለሚያገለግለው ካህን፣ “እግዚአብሔር ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እናገራለሁ” በለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚያን ወራት በሥልጣን ላይ ወዳለው ካህን ሄደህ እንዲህ በለው፦ ‘እኔ ዛሬ አስቀድሞ አምላክህ እግዚአብሔር ለእኛ ለልጆቻቸው እንዲሰጠን ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል ወደገባላቸው ምድር መግባቴን አረጋግጣለሁ።’

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በዚ​ያም ወራት ወደ​ሚ​ሆ​ነው ካህን መጥ​ተህ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አስ​ታ​ው​ቃ​ለሁ’ በለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በዚያም ወራት ወደሚሆነው ካህን መጥተህ፦ እግዚአብሔር ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አስታውቃለሁ በለው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 26:3
13 Cross References  

እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለማቅረብ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


እንግዲህ ዘወትር ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት አድርገን በእርሱ በኩል እናቅርብለት።


በእግዚአብሔርም ቤት ላይ ታላቅ ካህን ስላለን፥


እንዲህ ያለው ቅዱስ፥ ነቀፋ የሌለበት፥ ንጹሕ፥ ከኃጢአተኞች የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት ሊኖረን ይገባል፤


ሁለቱም ወገኖች በጌታ ፊት፥ በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ።


በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም፥ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።


በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”


ጌታ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ሰብል በኲራቱን ሁሉ ውሰድ፤ በቅርጫትም ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ጌታ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ።


“ካህኑም ቅርጫቱን ከእጅህ ተቀብሎ በጌታ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ለፊት ያስቀምጠዋል።


እነሆ፥ ምድሪቱን በፊታችሁ አኖራለሁ፥ ግቡ፥ ጌታ ለእነርሱ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውንም ምድር ውረሱ።’


Follow us:

Advertisements


Advertisements