ዘዳግም 26:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 በኀዘኔም ጊዜ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ወይም ንጹህ ባልነበርኩ ጊዜ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት መባ የለም፤ ለአምላኬ ጌታ ድምጽ ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 በሐዘን ላይ ሳለሁ፣ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ባልነጻሁበትም ጊዜ ከዚሁ ላይ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት ምንም ነገር የለም፤ አምላኬን እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በሞት ሐዘን ጊዜ ከእርሱ አልበላሁም፤ ንጹሕ ባልሆንኩበት ጊዜ ከእርሱ ምንም አላነሣሁም፤ ስለ ሞተ ሰው ለሚቀርብ መባ ከእርሱ ምንም አላቀረብኩም፤ ባዘዝከኝ መሠረት የአንተን የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 በኀዘኔም ጊዜ እኔ ከእርሱ አልበላሁም፤ ለርኩስም ነገር ከእርሱ የኀጢአት መሥዋዕት አልሠዋሁም፤ ከእርሱም አንዳች ለሞተ ሰው አልሰጠሁም፤ የአምላኬንም የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቼአለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ አድርጌአለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በኅዘኔ ጊዜ እኔ ከእርሱ አልበላሁም፥ ለርኩስነቴም ከእርሱ አላወጣሁም፥ ከእርሱም አንዳች ለሞተ ሰው አልሰጠሁም፤ የአምላኬንም የእግዚአሔርን ቃል ሰምቼአለሁ፥ ያዘዝኽኝንም ሁሉ አድርጌአለሁ። See the chapter |