Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 25:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሆኖም ግን አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ለማግባት ባይፈልግ፥ ሴትዮዋ በከተማዋ በር ወዳሉት ሽማግሌዎች ሄዳ፥ ‘የባለቤቴ ወንድም የወንድሙን ስም በእስራኤል ለማስጠራት አልፈለገም፤ የዋርሳነት ግዴታውንም አልፈጸመልኝም’ ትበላቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሆኖም ግን አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ለማግባት ባይፈልግ፣ ሴትዮዋ በከተማዪቱ በር ወዳሉት ሽማግሌዎች ሄዳ፣ “የባለቤቴ ወንድም የወንድሙን ስም በእስራኤል ለማስጠራት አልፈለገም፤ የዋርሳነት ግዴታውንም አልፈጸመልኝም” ትበላቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ነገር ግን የሟቹ ወንድም እርስዋን ለማግባት ባይፈልግ፥ ወደ ከተማይቱ መሪዎች ዘንድ ሄዳ ‘የባሌ ወንድም ግዴታውን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ ለሟቹ ወንድም በእስራኤል ሕዝብ መካከል ዘር ለመተካት ፈቃደኛ አልሆነም’ በማለት ታስረዳ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ያም ሰው የወ​ን​ድ​ሙን ሚስት ማግ​ባት ባይ​ወ​ድድ፥ ዋር​ሳ​ዪቱ በበሩ አደ​ባ​ባይ ወደ​ሚ​ቀ​መጡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሄዳ፦ ‘ዋር​ሳዬ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ለወ​ን​ድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእ​ኔም ጋር ሊኖር አል​ወ​ደ​ደም’ ትበ​ላ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳይቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ፦ ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔ ጋር ሊኖርም አልወደደም ትበላቸው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 25:7
4 Cross References  

ከዚያም የከተማው ሽማግሌዎች ሰው ጠርተው ያነጋግሩት፤ እርሱም፥ ‘እርሷን ላገባት አልፈልግም’ ብሎ በሐሳቡ ቢጸና፥


በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ፦ “እኛ ምስክሮች ነን፥ ጌታ ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ፥ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፥ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተልሔም ይጠራ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements