Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 24:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም ቢሆን፥ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ፤ የሰውን ነፍስ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆናልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም እንኳ ቢሆን፣ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ፤ የሰውን ነፍስ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆናልና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “ለአንድ ሰው ብድር በምታበድርበት ጊዜ የእህል ወፍጮውን ወይም መጁን መያዣ አድርገህ አትውሰድበት፤ ይህን ማድረግ ሕይወትን እንደ መያዣ አድርጎ እንደ መውሰድ ይቈጠራል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “የሰ​ውን ነፍስ እንደ መው​ሰድ ነውና ወፍጮ ወይም መጅ ስለ መያዣ ማንም አይ​ው​ሰድ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሰውን ነፍስ እንደ መውሰድ ነውና ወፍጮ ወይም መጅ ስለ መያዣ ማንም አይውሰድ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 24:6
9 Cross References  

“የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፤ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ፤” አላቸው።


“አንድን ከተማ ተዋግተህ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ ካደረግህ፥ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፈህ አታጥፋ፤ የእነርሱን ፍሬ መብላት ትችላለህና አትቁረጣቸው፤ ከበህ የምታጠፋቸው የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን?


እንግዲህ አሁን ልጁን ሳንይዝ ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ ብመለስ፥ ሕይወቱ ከልጁ ሕይወት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ስለ ሆነ፥


ከእንግዲህ ወዲህ በገና የሚመቱና የሚዘምሩ ሰዎች ድምፅ፥ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ሰዎች ድምፅ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ የማንኛውም ዕደ ጥበብ ብልሃተኛ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤


ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች አንዷ ትቀራለች።


“አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፥ ለጦርነት አይሂድ፤ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሠራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ እቤቱ ይቆይ፤ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።


“አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባርያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። በዚህ ዓይነት ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።


ከወንድሞችህ አላግባብ መያዣ ወስደሃል፥ የታረዙትንም ልብስ ዘርፈሃል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements