Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 22:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመንዝራውና አመንዝራይቱ ሁለቱም ይገደሉ። በዚህም ዓይነት ይህን ክፉ ነገር ከእስራኤል አስወግዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አንድ ሰው፣ ከሌላ ሰው ሚስት ጋራ ተኝቶ ቢገኝ፣ ዐብሯት የተኛው ሰውና ሴቲቱ ሁለቱም ይገደሉ፤ ክፉውን ከእስራኤል ማስወገድ አለብህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ሁለቱም ይገደሉ። በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከእስራኤል አስወግዱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “ማና​ቸ​ውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመ​ን​ዝ​ራ​ውና አመ​ን​ዝ​ራ​ዪቱ ሁለ​ታ​ቸው ይገ​ደሉ፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከእ​ስ​ራ​ኤል ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመንዝራውና አመንዝራይቱ ሁለታቸው ይሙቱ፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከእስራኤል ታስወግዳለህ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 22:22
11 Cross References  

“ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራይቱ ፈጽመው ይገደሉ።


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፥ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።


በአመንዝሮችና በደም አፍሳሽ ሴቶች ላይ የሚፈረደውን ፍርድ እፈርድብሻለሁ፥ የመዓትንና የቅንዓትን ደም አመጣብሻለሁ።


“‘አታመንዝር’ እንደተባለ ሰምታችኋል።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት አይቶ የተመኛት ሁሉ ከወዲሁ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሮአል።


ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥


ሴቲቱ ፀነሰች፤ ለዳዊትም፥ “አርግዣለሁ” ብላ ላከችበት።


ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ፥ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት፤ እንዲሁም ክፋቱን ከመካከልህ አስወግድ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements