ዘዳግም 22:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል በማስከፈል ለብላቴናይቱም አባት ይስጡት፥ እርሷም ሚስቱ ሆና ትኑር፥ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ይህ ሰው የአንዲት እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቷልና አንድ መቶ ሰቅል ብር ያስከፍሉት፤ ገንዘቡንም ለልጅቱ አባት ይስጡት፤ ሴቲቱም ሚስቱ ሆና ትኖራለች፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 በተጨማሪም አንድ መቶ ጥሬ ብር መቀጫ አስከፍለው ገንዘቡን ለልጅትዋ አባት ይስጡት፤ ያ ሰው ድንግል የሆነችውን የአንዲት እስራኤላዊት ልጃገረድ ስም አጒድፎአል፤ ከዚህም በቀር የእርሱ ሚስት ሆና ትኖራለች፤ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ሊፈታት አይገባም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል ያስከፍሉት፤ ለብላቴናዪቱም አባት ይስጡት፤ እርስዋም ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል ያስከፍሉት፥ ለብላቴናይቱም አባት ይስጡት፤ እርስዋም ሚስት ትሁነው፥ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም። See the chapter |