ዘዳግም 21:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ጌታ ሆይ፤ ስለ ተቤዥኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፤ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ።’ ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ተቤዠኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፤ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ።” ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እግዚአብሔር ሆይ፥ ከግብጽ ምድር ዋጅተህ ያወጣሃቸውን ሕዝብህን እስራኤልን ይቅር በል፤ እኛንም ይቅር በለን፤ ስለዚህም ስለ ፈሰሰው የንጹሕ ሰው ደም በኀላፊነት ተጠያቂዎች አታድርገን።’ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 አቤቱ፥ ከግብፅ ምድር የተቤዠኸውን ሕዝብህን እስራኤልን ይቅር በል፤ በሕዝብህም በእስራኤል ላይ የንጹሑን ደም በደል አትቍጠር’ ብለው ይናገሩ፤ ስለ ደሙም ይሰረይላቸዋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 አቤቱ፥ የተቤዠኸውን ሕዝብህን እስራኤልን ይቅር በል፤ በሕዝብህም በእስራኤል ላይ የንጹሑን ደም በደል አትቁጠር ብለው ይናገራሉ። ስለ ደሙም ይሰረይላቸዋል። See the chapter |