ዘዳግም 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 እንዲያገለግሉና በጌታ ስም እንዲባርኩ፥ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጉዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፥ አምላክህ ጌታ መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ፣ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጕዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፣ አምላክህ እግዚአብሔር መርጧቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እርሱን እንዲያገለግሉት፥ በእርሱ ስም እንዲባርኩ፥ የክርክርና የወንጀል ጉዳይ በእነርሱ እንዲወሰን አምላክህ እግዚአብሔር ካህናቱን የሌዊን ልጆች ስለ መረጣቸው ወደ አስከሬኑ ይቅረቡ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የሌዊ ልጆች ካህናትም ይቀርባሉ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉ፥ በስሙም እንዲባርኩ አምላክህ እግዚአብሔር መርጦአቸዋልና፤ በእነርሱም ቃል ክርክር ሁሉ ጕዳትም ሁሉ ይቆማልና፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የሌዊ ልጆች ካህናትም ይቀርባሉ፤ በፊቱ እንዲያገልግሉ፥ በስሙም እንዲባርኩ አምላክህ እግዚአብሔር መርጦአቸዋልና፥ በእነርሱም ቃል ክርክር ሁሉ ጉዳትም ሁሉ ይቈረጣልና፤ See the chapter |