Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 21:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፤ አንደኛዋን የሚወዳት፥ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፥ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት በኩር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፣ አንደኛዋን የሚወድዳት፣ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፣ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት በኵር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወድዳት ሚስቱ ቢሆን፣

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “አንድ ሰው ሁለት ሚስቶችን አግብቶ አንደኛይቱን አፍቅሮ ሌላይቱን ባያፈቅርና ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ቢወልዱለት፥ ምናልባት የመጀመሪያው ልጅ የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “ለአ​ንድ ሰው አን​ዲቱ የተ​ወ​ደ​ደች፥ አን​ዲ​ቱም የተ​ጠ​ላች ሁለት ሚስ​ቶች ቢኖ​ሩት፥ ለእ​ር​ሱም የተ​ወ​ደ​ደ​ችው፥ ደግ​ሞም የተ​ጠ​ላ​ችው ልጆ​ችን ቢወ​ልዱ፥ በኵ​ሩም ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደው ልጅ ቢሆን፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኩሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥

See the chapter Copy




ዘዳግም 21:15
8 Cross References  

ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህን ደገመኝ አለች፥ ስሙንም ስምዖን ብላ ጠራችው።


ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፥ እርሷንም ይወድዳት ስለ ነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።


ያዕቆብም ራሔልን ወደደ፥ እንዲህም አለ፦ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ።”


ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፥ የብኩርናን መብት ከማይወዳት ሚስቱ ከወለደው በኩር ልጅ ገፎ፥ ከሚወዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ፥ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤


እርሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ስማቸውም አንዲቱ ሐና፥ ሁለተኛዪቱም ጵኒና ነበር። ጵኒና ልጆች ነበሯት፤ ሐና ግን ምንም ልጅ አልነበራትም።


ሮብዓምም ንጉሥ ሊያደርገው አስቦአልና የመዓካን ልጅ አብያን በወንድሞቹ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements