Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አስቀድሞ ታላቅና ብዙ ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች በቁመት የረዘሙ ኤሚማውያን በዚያ ይቀመጡ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚያም ጠንካራና ቍጥራቸው የበዛ እንዲሁም እንደ ዔናቃውያን ረዣዥም የሆኑ ኤሚማውያን ይኖሩ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 [ኤሚም ተብለው የሚጠሩ ብርቱ የሆኑ ብዙ ሕዝብ በዔር ይኖሩ ነበር፤ እነርሱም ግዙፋን እንደ ሆኑት እንደ ዐናቅ ነገዶች ቁመተ ረጃጅሞች ነበሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ ሕዝብ ኀያ​ላ​ንም የሆኑ ኦሚ​ና​ው​ያን አስ​ቀ​ድሞ በዚያ ይቀ​መጡ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አስቀድሞ ታላቅና ብዙ ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች በቁመት የረዘሙ ኤሚማውያን በዚያ ይቀመጡ ነበር።

See the chapter Copy




ዘዳግም 2:10
5 Cross References  

በዓሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፥ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፥


እነርሱም ደግሞ እንደ ዔናቅ ልጆች ራፋይም ይባሉ ነበር፥ ሞዓባውያን ግን ኤሚም ይሉአቸዋል።


በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብጽ ካለችው ከጣኔዎእ ከሰባት ዓመት በፊት የተቈረቈረች ከተማ ነበረች።


ወዴትስ እንወጣለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል፥ ከተሞቹም ታላላቆች የተመሸጉም እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፥’ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አወኩት።


ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢበኖብ የተባለ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements