Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 19:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “አምላክህ ጌታ ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ ጌታ እግዚአብሔር በሚደመስሳቸውና አንተም እነርሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጥበት ጊዜ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አምላክህ እግዚአብሔር ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ በሚደመስሳቸው ጊዜና አንተም እነርሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጥበት ጊዜ፣

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር የሚኖሩትን ሕዝቦች ደምስሶ ከተሞቻቸውንና ቤቶቻቸውንም ወርሰህ በዚያ መኖር በምትጀምሩበት ጊዜ፥

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ራ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ጥ​ህን አሕ​ዛብ ባጠ​ፋ​ቸው ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አምላክህ እግዚአብሔር ምድራቸውን የሚሰጥህን አሕዛብ ባጠፋ ጊዜ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸውም በተቀመጥህ ጊዜ፥

See the chapter Copy




ዘዳግም 19:1
11 Cross References  

“የምትወሯቸውንና የምታስለቅቋቸውን አሕዛብ አምላካችሁ ጌታ ከፊታችሁ ያስወግዳቸዋል፤ ባስወጣችኋቸውና በምድራቸው በተቀመጣችሁ ጊዜ ግን፥


“ጌታ አምላክህ ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ፥ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባስገባህ ጊዜ፥ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥


“አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፥ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፥ ‘በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፥ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል፥


“የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ፥ እንድትወርሷት በሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ ሁሉ፥ በጥንቃቄ ልትከተሏቸው የሚገባችሁ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።


ሳይሸምቅበት፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ድንገት በእጁ ቢጥለው፥ የሚሸሽበት ስፍራ እኔ አዘጋጅልሃለሁ።


በስሕተት ነፍስ የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ የመማፀኛ ከተሞች እንዲሆኑላችሁ ለእናንተ ከተሞችን ትመርጣላችሁ።


ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልቆፈርካቸውም የተቆፈሩ ጉድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም የወይን ተክልና የወይራ ዛፎች፥ ስትበላና ስትጠግብ፥


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ጌታም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ከተሞች ሰጠኋችሁ፥ ተቀመጣችሁባቸውም፤ ካልተከላችኋቸውም ከወይንና ከወይራ በላችሁ።’


Follow us:

Advertisements


Advertisements