Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 18:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ፥ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ፣ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች የሚፈጽሙትን አጸያፊ ልማድ ሁሉ አትከተል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ እነ​ዚያ አሕ​ዛብ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኵ​ሰት ታደ​ርግ ዘንድ አት​ማር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኩሰት ታደርግ ዘንድ አትማር።

See the chapter Copy




ዘዳግም 18:9
11 Cross References  

ስለዚህ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ የተደረገውን ጸያፍ ወግ ሁሉ ፈጽሞ እንዳታደርጉ፥ በእርሱም ራሳችሁን ፈጽሞ እንዳትረክሱ ሥርዓቴን ጠብቁ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”


“ጌታ አምላክህ ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ፥ በልብህ፥ ‘እንድንወርሳት ወደዚች ምድር ጌታ ያስገባኝ በጽድቄ ምክንያት ነው’ አትበል፤ ጌታ እነዚህን ሕዝቦች ከፊትህ ያስወጣቸው ስለ ኃጢአታቸው ነው።


ምድራቸውን እንድትወርስ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፥ ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ ሕዝቦች ኃጢአት ምክንያትና፥ ለአባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብ፥ ጌታ የማለላቸውን ቃል እንዲፈጸም ነው።


ሕዝቡ ወደ ፊት እየገፋ በመጣ ጊዜ ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸውን የአሕዛብን መጥፎ ልማድ ተከተሉ፤ እንዲሁም የእስራኤል ነገሥታት ያሠራጩትን መጥፎ ልማድ ተቀባዮች ሆኑ።


አለበለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩሃል፤ በጌታ በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ትሠራለህ።


እግዚአብሔር ከምድሪቱ ነቃቅሎ ያስወጣቸውን የአረማውያንን ሕዝብ ልማድ በመከተል በአሕዛብ መሠዊያዎች ሁሉ ላይ ዕጣን አጠኑ፤ በዚህም ክፉ ሥራቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፤


ደግሞም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ዐጠነ፤ ጌታ ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብም ክፉ ልማድ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።


ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት ሁሉ በመከተል መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ጌታ ራሱ የቀደሰውን የጌታን ቤት አረከሱ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፥ ከሰማይ ምልክቶችም የተነሣ አትፍሩ፤ አሕዛብ ከእነርሱ የተነሣ ይፈራሉና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements