ዘዳግም 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፥ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያዳምጣሉ፤ አንተ ግን ይህን እንድታደርግ ጌታ እግዚአብሔር አልፈቀደልህም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፣ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያደምጣሉ፤ አንተ ግን ይህን እንድታደርግ አምላክህ እግዚአብሔር አልፈቀደልህም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ከዚህ በኋላ ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሀገራቸውን አስለቅቀህ የምትወርስባቸው ሕዝቦች ሟርተኝነትንና ጥንቈላን ይወዳሉ፤ አንተ ግን እግዚአብሔር አምላክህ ይህን እንድታደርግ አይፈቅድም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 አንተ የምትወርሳቸው እነዚህ አሕዛብ ሞራ ገላጮችንና ምዋርተኞችን ያዳምጣሉ፤ ለአንተ ግን እንዲህ አይደለም፤ አምላክህ እግዚአብሔር አልፈቀደምና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የምትወርሳቸው እነዚህ አሕዛብ ሞራ ገላጮችንና ምዋርተኞችን ያዳምጣሉ፤ አንተ ግን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከልክሎሃል። See the chapter |