ዘዳግም 17:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 እርሱና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ረጅም ዘመን እንዲገዙ፥ ከሕጉ ቀኝም ግራም አይበል፤ ራሱን ከሌሎች ወንድሞቹ በላይ የተሻለ አድርጎ አይኩራ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 እርሱና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ፣ ከሕጉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አይበል፤ ራሱን ከሌሎች ወንድሞቹ በላይ የተሻለ አድርጎ አይቍጠር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ራሱንም ከወገኖቹ ከእስራኤላውያን እበልጣለሁ ብሎ እንዳይታበይና ከእግዚአብሔርም ትእዛዞች እንዳይርቅ ይጠብቀዋል። ይህን ቢያደርግ ለብዙ ዘመን ይነግሣል፤ ልጆቹም በእስራኤል ላይ ለብዙ ዘመን ይነግሣሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኰራ፥ የአምላኩ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዳይተው፥ ቀኝና ግራም እንዳይል፥ እርሱም ልጆቹም በእስራኤል ልጆች መካከል ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ። See the chapter |