ዘዳግም 17:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 አንተም ጌታ በመረጠው ስፍራ እነርሱ በሚሰጡህ ውሳኔ መሠረት ፈጽም፤ ለመፈጸም የሚሰጡህን መመሪያ ሁሉ በጥንቃቄ አድርግ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 አንተም እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ እነርሱ በሚሰጡህ ውሳኔ መሠረት ፈጽም። እንድትፈጽም የሚሰጡህን መመሪያ ሁሉ በጥንቃቄ አድርግ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እግዚአብሔር በሚመርጠው ቦታ ሆነው የሚሰጡህን ውሳኔ በትክክል እሥራ ላይ አውል፤ እነርሱም የሚነግሩህን በጥንቃቄ ጠብቅ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ እንደ ነገሩህ ቃል ታደርጋለህ፤ ያስተማሩህንም ሕጉን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ የነገሩህን የፍርድ ነገር ታደርጋለህ፤ እንዳስተማሩህም ታደርግ ዘንድ ጠብቅ። See the chapter |