ዘዳግም 15:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አምላክህ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ይባርክሃል፥ አንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ ከማንም ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብን ትገዛለህ ማንም ግን አንተን አይገዛህም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ስለሚባርክህ፣ አንተ ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ እንጂ ከማንም አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብን ትገዛለህ እንጂ ማንም አንተን አይገዛህም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ይባርክሃል፤ አንተ ለብዙ ሕዝቦች ገንዘብ ታበድራለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ከማንኛውም ሰው አትበደርም፤ አንተ በብዙ ሕዝቦች ላይ የበላይነት ይኖርሃል፤ በአንተ ላይ ግን ማንም የበላይ አይሆንም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ ይባርክሃል፤ ለብዙ አሕዛብም ብዙ ታበድራለህ፤ አንተ ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብንም ትገዛለህ፤ አንተን ግን አይገዙህም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 አምላክህም እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠህ ይባርክሃል፤ ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ፥ አንተ ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብንም ትገዛለህ፥ አንተን ግን አይገዙህም። See the chapter |