Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 15:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የአገልጋይህን የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፥ አንድ የቅጥር ሠራተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና፤ እርሱን ነጻ ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ። ጌታ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አገልጋይህን ዐርነት ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ፤ የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፣ አንድ የቅጥር ሠራተኛ የሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና። አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እርሱንም ነጻ ባወጣኸው ጊዜ አንድ ተቀጣሪ ለስድስት ዓመት ከሚሰጥህ እጥፍ አገልግሎት ስለ ሰጠህ ቅር አይበልህ። እንግዲህ ይህን አድርግ፤ እግዚአብሔርም በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ሱ​ንም አር​ነት ባወ​ጣ​ኸው ጊዜ የም​ን​ደ​ኝ​ነ​ቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድ​ርጎ ስድ​ስት ዓመት አገ​ል​ግ​ሎ​ሃ​ልና አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ሠ​ራው ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሱንም አርነት ባወጣኸው ጊዜ የምንደኝነቱን ሥራ ሁለት እጥፍ አድርጎ ስድስት ዓመት አገልግሎሃልና አይክበድህ፤ አምልካህም እግዚአብሔር በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።

See the chapter Copy




ዘዳግም 15:18
6 Cross References  

ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፤


አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እንደ ተቀጣሪ ደሞዝተኛ የሞዓብ ክብር፥ ምንም ያህል ሕዝቡ ቢበዛ፥ በሦስት ዓመት ውስጥ ይዋረዳል፤ የሚተርፈውም ሕዝብ እጅግ ጥቂትና ደካማ ይሆናል።”


ጆሮውን ከቤትህ መዝጊያ ላይ በማስደገፍ በወስፌ ትበሳዋለህ፤ ከዚያም ዕድሜ ልኩን አገልጋይህ ይሆናል። በሴት አገልጋይህም ላይ እንደዚሁ አድርግ።


“የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎችህን ተባዕት በኩር ሁሉ ለጌታ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ። የበሬህን በኩር አትሥራበት፤ የበግህንም በኩር አትሸልት፤


ይልቅስ ያለ ቅሬታ በለጋስነት በልግስና ስጠው፤ ከዚህም የተነሣ ጌታ አምላክህ በሥራህ ሁሉና እጅህ ባረፈበት በማናቸውም ነገር ይባርክሃል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements