ዘዳግም 11:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ይህን ካደረጋችሁ፥ ጌታ ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ይህን ካደረጋችሁ፣ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ይህን ብታደርግ እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል በገባላቸው ምድር የአንተና የልጆችህ ዘመን ከምድር በላይ እንዳለው ሰማይ ይረዝማል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 በምድር ላይ የሰማይን ዘመን ያህል ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር ዘመናችሁ የልጆቻችሁም ዘመን ይረዝም ዘንድ፤ See the chapter |