ዘዳግም 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ተመልሳችሁ ተጓዙ፥ ወደ ተራራማው ወደ አሞራውያን አገር፥ ወደ አጎራባቾቹም በዓረባም በደጋውና በቆላው ሁሉ፥ በኔጌብም በባሕርም ዳር ወዳሉ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስም እስከ ታላቁ ወንዝም እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ሰፈር ነቅላችሁ ወደ ኰረብታማው የአሞራውያን አገር ጕዞ ቀጥሉ፤ ከዚያም በዓረባ፣ በተራሮቹ፣ በምዕራብ ኰረብቶች ግርጌ፣ በኔጌብና በባሕሩ ዳርቻ ወዳሉት አጐራባች ሕዝቦች ሁሉ ሂዱ፤ እንዲሁም ወደ ከነዓናውያን ምድርና ወደ ሊባኖስ፣ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ዝለቁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ሰፈራችሁን ነቅላችሁ ወደ ተራራማው የአሞራውያን አገር፥ ወደ ጐረቤትም ወደ አራባ በደጋውና በቈላው አገር፥ በኔጌብ፥ በሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ በኩል፥ በከነዓናውያን አገርና በሊባኖስ በኩል አድርጋችሁ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ተመልሳችሁ ተጓዙ፤ ወደ አሞራውያን ተራራ፥ ወደ አረባም ሀገሮች ሁሉ፥ በተራራውም፥ በሜዳውም፥ በሊባም፥ በባሕርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስም ፊት ለፊት እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ተመልሳችሁ ተጓዙ፤ ወደ ተራራማው ወደ አሞራውያን አገር ወደ ድንበሮቹም ሁሉ፥ በዓረባም በደጋውም በቈላውም በደቡብም በባሕርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስም እስከ ታላቁ ወንዝም እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ። See the chapter |