Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 1:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 “እናንተም፦ ‘ጌታን በድለናል፥ ጌታ አምላካችን ልክ እንዳዘዘን፥ እንወጣለን እንዋጋለንም’ ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር መውጣትን አቀለላችሁት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 እናንተ፣ “በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ባዘዘንም መሠረት ወጥተን እንዋጋለን” ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ወደ ተራራማው አገር መሄድ ቀላል መስሎ ስለ ታያችሁ፣ እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ ተነሣችሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 “እናንተም ‘ሙሴ ሆይ፥ እኛ እግዚአብሔርን በድለናል፤ አሁን ግን አምላካችን እግዚአብሔር ባዘዘን መሠረት እንዋጋለን’ ብላችሁ መለሳችሁ፤ ኮረብታማይቱን አገር መውረር ቀላል መስሎአችሁ ከእናንተ እያንዳንዱ ለውጊያ ተዘጋጀ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 “እና​ን​ተም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ናል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን ሁሉ እን​ወ​ጣ​ለን፤ እን​ዋ​ጋ​ማ​ለን ብላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ሁ​ልኝ። ከእ​ና​ን​ተም ሰው ሁሉ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ያዘ፤ ወደ ተራ​ራም ወጣ​ችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እናንተም፦ እግዚአብሔርን በድለናል፤ አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ሁሉ እንወጣለን፥ እንዋጋማለን ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር መውጣትን አቀለላችሁት።

See the chapter Copy




ዘዳግም 1:41
4 Cross References  

የሰው ስንፍና መንገዱን ታጣምምበታለች፥ ልቡም በጌታ ላይ ይቈጣል።


በለዓምም የጌታን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ ልትቃወመኝ መቆምክን አላወቅሁም፤ እንግዲህም ይህ አሁን በፊትህ ክፉ የሆነ ነገር ቢሆን እመለሳለሁ።”


ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውንም በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲገደል ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements