ዘዳግም 1:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 “ደግሞ፦ ‘ይማረካሉ ያላችኋቸው ሕፃናቶቻችሁ፥ ዛሬም መልካሙን ከክፉ መለየት የማይችሉ ልጆቻችሁ፥ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ፥ ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ፥ ይወርሱአታልም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም39 ይማረካሉ ያላችኋቸው ታናናሾች፣ ክፉና በጎውን ለይተው የማያውቁት ልጆቻችሁ ምድሪቱን ይገቡባታል፤ ለእነርሱም እሰጣቸዋለሁ፤ እነርሱም ይወርሷታል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 “ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለሁላችንም እንዲህ አለ፤ ‘በጠላቶቻችን ይማረካሉ ያላችኋቸው ሕፃናትና ክፉና ደጉን ለይተው የማያውቁ ልጆቻችሁ ብቻ ወደዚያች ምድር ይገባሉ፤ ምድሪቱን ለእነርሱ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ይወርሱአታል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 ደግሞ፦ ይማረካሉ ያላችኋቸው ልጆቻችሁ፥ ዛሬም መልካሙን ከክፉ መለየት የማይችሉ ሕፃኖቻችሁ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ፤ ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ፤ ይወርሱአታልም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 ደግሞ፦ ለምርኮ ይሆናሉ ያላችኋቸው ሕፃናቶቻችሁ፥ ዛሬም መልካሙን ከክፉ መለየት የማይችሉ ልጆቻችሁ፥ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ፥ ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ ይወርሱአታልም። See the chapter |