ዘዳግም 1:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ በምድረ በዳም፥ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ፥ ጌታ አምላካችሁ እንዴት እንደተንከባከባችሁ አይታችኋል።’ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 በምድረ በዳው እንደ አደረገው ሁሉ። በዚያም አባት ልጁን እንደሚሸከም፣ እናንተን አምላካችሁ እግዚአብሔር እዚህ ስፍራ እስክትደርሱ በመጣችሁበት መንገድ ሁሉ እንዴት እንደ ተሸከማችሁ አይታችኋል።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 እናንተ ወደዚህ ቦታ እስክትመጡ ድረስ አንድ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳው እንደ ተንከባከባችሁ አይታችኋል።’ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ ሰው ልጁን እንዲመግብ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳ እንደመገባችሁ እናንተ አይታችኋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ ሰው ልጁን እንዲሸከም አምላክህ እግዚአብሔር እንደተሸከመህ አንተ አይተሃል። See the chapter |