Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




አሞጽ 9:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ጠፈሩንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ጌታ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መኖሪያውን በሰማይ የሚሠራ፣ መሠረቱንም በምድር የሚያደርግ፣ የባሕርን ውሃ የሚጠራ፣ በምድርም ገጽ ላይ የሚያፈስስ፣ እርሱ ስሙ እግዚአብሔር ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 መኖሪያውን በሰማያት ያደረገ፥ ጠፈርን ከምድር በላይ ያጸና፥ የባሕሩን ውሃ አዞ በምድር ላይ እንዲፈስ የሚያደርግ፥ ስሙ እግዚአብሔር ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አዳ​ራ​ሹን በሰ​ማይ የሠራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም በም​ድር ላይ የመ​ሠ​ረተ፥ የባ​ሕ​ር​ንም ውኃ ጠርቶ በም​ድር ፊት የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ጠፈሩንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሰው እርሱ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው።

See the chapter Copy




አሞጽ 9:6
9 Cross References  

ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረ፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጥ፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልም፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸው እርሱ፥ ስሙ ጌታ ነው።


“እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የልቡንም ሐሳብ ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ ጌታ ነው።”


እልፍኙን በውኃ የሚሠራ፥ ሠረገላውን ደመና የሚያደርግ፥ በነፋስ ክንፍም የሚሄድ፥


ተራሮችን ከላይ የምታጠጣቸው፥ ከሥራህ ፍሬ ምድር ትጠግባለች።


በውኑ እኔን አትፈሩምን? ይላል ጌታ፤ ከፊቴስ አትደነግጡምን? አልፎት እንዳይሻገር አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ድንበር አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፈውም።


ሰማያትና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ እነሆ ተፈጸሙ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements