አሞጽ 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ድሀውን በብር ችግረኛውንም በአንድ ጥንድ ጫማ እንገዛለን፥ የስንዴውን ገለባ እንሸጣለን።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ድኻውን በብር፣ ችግረኛውንም በጥንድ ጫማ እንገዛለን፤ ግርዱን እንኳ በስንዴ ዋጋ እንሸጣለን። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የስንዴውን ግርድ እንኳ እንሸጣለን፤ ድኻውን በብር ችግረኛውንም በአንድ ጥንድ ነጠላ ጫማ እንገዛለን።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ድሃውን በብር፥ ችግረኛውንም በአንድ ጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ፥ በእህላችንም ንግድ እንድንጠቀም ሰንበት መቼ ያልፋል? የምትሉ እናንተ ሆይ! ይህን ስሙ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ድሀውን በብር ችጋረኛውንም በአንድ ጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ፥ የስንዴውን ግርድ እንሸጥ ዘንድ ስንዴውን እንድንሸምት ሰንበት መቼ ያልፋል? የምትሉ እናንተ ሆይ፥ ይህን ስሙ። See the chapter |