Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




አሞጽ 8:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የጌታን ቃል ለመሻት ይሯሯጣሉ፥ ነገር ግን አያገኙትም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል በመሻት፣ ከባሕር ወደ ባሕር፣ ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይንከራተታሉ፤ ነገር ግን አያገኙትም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሕዝቡ ሁሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ፥ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የእግዚአብሔርንም ቃል ለማግኘት በሁሉ ቦታ ይንከራተታሉ፤ ነገር ግን አያገኙም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከባ​ሕ​ርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰ​ሜ​ንም እስከ ምሥ​ራቅ ድረስ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ለመ​ሻት ይር​ዋ​ር​ዋ​ጣሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ት​ምም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ለመሻት ይርዋርዋጣሉ፥ አያገኙትምም።

See the chapter Copy




አሞጽ 8:12
14 Cross References  

ከእኔ ጋር ያልሆነ ተቃዋሚዬ ነው፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብ ደግሞ ይበትናል።


ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል አያገኛትም፥ ለአስተዋይ ግን እውቀትን ማግኘት አያስቸግረውም።


ቁርባናችሁን ባቀረባችሁ ጊዜ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ትረክሳላችሁን የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ከእናንተስ ዘንድ እጠየቃለሁን? እኔ ሕያው ነኛና ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤


የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ተናገራቸው፥ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ እኔን ልትጠይቁ መጣችሁን? እኔ ሕያው ነኝ፥ ለእናንተ አልጠየቅም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ ጌታን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የጌታ ቃል ዘወትር የሚሰማ አልነበረም፤ ራእይም አይታይም ነበር።


ራእይ ከሌለ ሕዝብ ከመስመር ይወጣል፥ ሕግን የሚጠብቅ ግን ብፁዕ ነው።


የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፥ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።


ጌታንም ለመሻት በጎቻቸውንና በሬዎቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተመልሶአልና አያገኙትም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements