አሞጽ 6:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ወደ ካልኔ እለፉና ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ወደ ካልኔ ሂዱ፤ እርሱንም ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ ወደ ፍልስጥኤም ከተማ ወደ ጋትም ውረዱ፤ እነዚህ ከሁለቱ መንግሥታታችሁ ይሻላሉን? የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣልን? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እስቲ ወደ ካልኔ ከተማ ሄዳችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም አልፋችሁ “ሐማት” ተብላ ወደምትጠራው ታላቂቱ ከተማና የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወደሆነችው ወደ ጋት ውረዱ፤ እናንተ ከእነርሱ ትበልጣላችሁን? ግዛታችሁስ ከእነርሱ ግዛት ይበልጣልን? See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ወደ ካልኔ ተሻግራችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ኤማትራባ እለፉ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይበረታሉ፤ ድንበራቸውም ከድንበራቸው ይሰፋልና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ወደ ካልኔ አልፋችሁ ተመልከቱ፥ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፥ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፥ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን? See the chapter |