አሞጽ 5:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለአንድነት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልቀበለውም፤ ከሠቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልመለከተውም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል መባ ብታቀርቡልኝ እንኳ አልቀበላችሁም፤ ለደኅንነት መሥዋዕት ወደምታቀርቡልኝ የሰቡ ፍሪዳዎችም አልመለከትም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ የድኅነት መሥዋዕታችሁንም አልመለከትም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፥ ለምስጋና መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም። See the chapter |